Seattle Public Schools

በ SPS አሁን ይመዝገቡ!

Summary: ጅዎ ነሐሴ 31 ላይ 5 ዓመት ይሆነዋል(ይሆናታል)? ስለዚህ በሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ወደ ኪንደርጋርተን ለመመዝገብ ጊዜው አሁን ነው።!

የሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (SPS) 

እንኳን ወደ ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች በደህና መጡ! ወረዳችን ወላጆች ታላላቅ የትምህርት ባለሙያዎችን : ጠንካራ የትምህርት ፕሮግራሞችንና ተሳታፊ ማህበረሰብ የሚያገኙበት የአካባቢና አማራጭ ት/ቤቶች ያሉት ነው:: 

ተማሪዎቻችን ቅድሚያ ይሰጣቸዋል 

በ SPS, ዋናው ስራችን ጸረ-ዘረኝነትን የሚያራምድ የትምህርት ስርዓትን የሚያማክል የተማሪዎች ትምህርትን በመደገፍ እያንዳንዱ ተማሪ ለኮሌጅ፣ ለስራ እና ለህይወት ዝግጁ ሆኖ እንዲመረቅ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ የኛ ኃላፊነት እንደሆነ እናምናለን።  

በሲያትል የህዝብ ት/ቤቶች ይመዝገቡ! 

ነሃሴ 31 ላይ ልጅዎት 5 ዓመት ይሞላዋል/ይሞላታል? ቤተሰብዎ ለሲያትል አዲስ ነው? ከሆነ ለትምህርት ቤት የመመዝገቢያው ጊዜ አሁን ነው!  

ቀደም ብለው በመመዝገብ፣ ተማሪዎች በክፍት የምዝገባ ወቅት (ከፌብሩዋሪ 1-28) አስፈላጊ ግብዓቶችን እና ከተመደቡበት የመማሪያ ትምህርት ቤት ውጪ ላሉ ሌሎች ትምህርት ቤቶች የማመልከት እድል ያገኛሉ። 

ለመጪው የት/ዘመን አዲስ የተማሪ ምዝገባ ጃንዋሪ 3 ይጀመራል::  

ሁሉም ምዝገባ ኦንላይን በ ይከናወናል:: 

ልንረዳዎት እንችላለን:: የቋንቋ ድጋፍ በ ስፓኒሽ: ኦሮሞ: ቻይንኛ: ቬትናሚዝ: አማርኛ እና ሶማሊ ይኖራል:: በ ጆንስታንፎርድ አድራሻችን 2445 3rd Ave S, Seattle, 98134 ይጎብኙን::   

ሰዓት: ከሰኞ – ዓርብ: ጥዋት ከ9:00 ሰዓት – ከሰዓት በኋላ 5:00 ሰዓት 

ጥያቄ ወይም አስተያየት አልዎት? በ admissions@dlokoko.com ወይም በ 206-252-0760 ያግኙን:: 

You may also be interested in

An illustration of a calendar

የ2024-25 ቁልፍ ቀኖች

የ2024-25 የትምህርት ዘመን ቀናት…

ዳንድ ትምህርት ቤቶች የመጨረሻ የትምህርት ቀን ዝማኔዎች

በጥር 2022 ባጋጠመው የትምህርት ቀኖች መዘጋት ምክንያት በርካታ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የማካካሻ ቀናት ያስፈልጋቸዋል።…